ጣና ሃይቅ
የአባይ ወንዝ መነሻ ሆኖ የሚጠቀሰው ጣና ሃይቅ ከኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ ነው፡፡ ጣና ሃይቅ ስያሜን ያገኘው አመቤታችን በስደት ዘመኗ በጣና ቂርቆስ ገዳም የ3 ወር ከ10 ቀን ቆይታዋን አጠናቃ ወደ ገሊላ ናዝሬት ይመለሱ ዘንድ ይመራቸው የነበረው መልዓኩ ገብርኤል ለአረጋዊ ዮሴፍ በህልም ተገልጦ “ህፃኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ አገራችሁ ሂዱ” ብሎ ስለነገረው ቅዱስ ዮሴፍም ወደ ህፃኑ በመቅረብ “ፀአና በደመና” (በደመና ጫናት) ባለው ጊዜ የገዳሙና የሃይቁ ስም ጣና ተባለ ተብሎ ይተረካል፡፡
የኮሌራ በሽታ መንስኤውና መከላከያው
ኮሌራ ‹‹ቪብሪዮ ኮሌራ›› በሚባል መርዛማ ባክቴሪያ የሚመጣ የአንጀት ኢንፌክሽን ሲሆን አጣዳፊ ተቅማጥ የሚያስከትል በሽታ ነው። እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ በአለም ዙሪያ ከ1 ነጥብ 3 እስከ 4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች በየአመቱ በኮሌራ እንደሚያዙና ከእነዚህም መካከል ከ21ሺ እስከ 143ሺ የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በዚህ በሽታ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡
