የማርበርግ ቫይረስ
የማርበርግ ቫይረስ ተላላፊ የሆነ በሽታ ሲሆን በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልማሬድ ከተሞች ተከስቷል፡፡ ዝርያውም ፊሎቫይረስ በመባል የሚመደብ ሲሆን ከኢቦላ ቫይረስ ጋር ይቀራረባል።
የማርበርግ ቫይረስ ስርጭት የሚጀምረው በቫይረሱ ከተያዙ የሌሊት ወፎች እና አካባቢያቸው ወደ ሰው ሲተላለፍ ነው። የሌሊት ወፍ በሚገኙበት ዋሻ ውስጥ የማእድን ቁፋሮ ስራ የሚሰሩ ስዎች፣ ጎብኝዎች ለቫይረሱ ሊጋለጡ ይችላሉ። በሌሊት ወፍ ሽንት፣ ኩስ እና ምራቅ የተበከሉ ነገሮችም ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። ዋና የቫይረሱ ማስተላለፊያ የሌሊት ወፍ ቢሆንም ዝንጀሮዎች እና አሳማዎችም አንዳንዴ ጊዜያዊ የቫይረሱ መሸጋገሪያ ሊሆኑ ይችላሉ የሚሉ ጥናቶች አሉ።
ለ20ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሄር ብሄረሰቦች በዓል አከባባር
ለ20ኛጊዜ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን “ዲሞክራስያዊ መግባባት ለህብረ ብሄራዊ አንድነት” በሚል መልዕክት፤ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሆሳና ከተማ ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል፣ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በየዓመቱ የሚከበረ የህዝቦች ትስስርን በማጠናከር እና በማጎልበት ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን በጠንካራ መሰረት ላይ እንዲገነባ ከፍተኛ ፋይዳ ያለዉ በመሆኑ ክብረ በዓሉ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ባህላቸውንና ማንነታቸውን ለማስተዋወቅ ዕድል ይፈጥራል፡፡ በ1987ዓ.ም የፀደቀው የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የብሔር ብሔረሰቦችን መብት የሚያረጋግጥ፣ የራስን ዕድል በራስ የመወሰንና መብትን የሚጐናፅፍ በመሆኑና የባሕላዊ እሴቶቻችን ለሚዲያ ተደራሽ የምናደርግበት ነው፡፡
ህዳር ሲታጠን
ኅዳር የወር ስም ሆኖ በጥቅምት ወር እና በታኅሣሥ ወር መሀከል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ ሦስተኛው የወር ስም ነው።«ኅዳር» ከግዕዙ «ኅደረ» ከሚለው ግስ የተገኘ ነው።በዚህ ወር በምዕራባዉያን አቆጣጠር በ1918 ዓ.ም በአንደኛዉ የአለም ጦርነት መባቻ አካባቢ ከመካከለኛዉ ምስራቅ በድንገት ተነስቶ ቀስበቀስ ከቦታ ቦታ እየተላለፈ አለምን አዳርሶ ለ200 ሚሊዮን ሰዎች መጥፊያ መንስኤ የሆነዉ ስፓኒሽ ፍሉ ወይም የኢንፎሎዌንዛ የተባለዉ በሽታ ከላይ በተጠቀሰዉ ዓመተ ምህረት በህዳር ወር በኢትዮጵያ ግዛት ዉስጥ ተዳርሶ የህዳር በሽታ በሚል ስያሜ ስፍር ቁጥር የሌለዉ የሰዉ ህይወት አጥፍቷል፡፡
የወባ በሽታ
የወባ በሽታ በዓይን በማይታይ የደም ጥገኛ ተህዋስያን በሆኑ ፕላዝሞዲየም በሚባሉ የፕሮቶዝዋ ዝርያዎች ምክንያት የሚመጣ በሽታ ሲሆን በዋናነት አኖፊለስ በምትባል ሴት ትንኝ ንክሻ አማካኝነት ከበሽተኛ ወደ ጤነኛ ሰው ይተላለፋል፡፡አንዳንድ ጊዜ ምልክቶቹ ከ48 እስከ 72 ሰዓት እየቆዩ በድጋሚ ይከሰታሉ፡፡ይህን የሚወስነው ግለሰቡን ያጠቁት ተሕዋስያን ዓይነትና በበሽታው ተይዞ የቆየበት ጊዜ ነው።በሽታው በአብዛኛው የክረምት ወራት መውጣትን ተከትሉ ከመስከርም እስከ ታህሳስ በከፍተኛ ደረጃ የሚተላለፍ ሲሆን በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ከበልግ ዝናብ በኋላ ከሚያዚያ እስከ ሰኔ በዝቅተኛ ደረጃ ይተላለፋል፡፡
ጣና ሃይቅ
የአባይ ወንዝ መነሻ ሆኖ የሚጠቀሰው ጣና ሃይቅ ከኢትዮጵያ ትልቁ ሃይቅ ነው፡፡ ጣና ሃይቅ ስያሜን ያገኘው አመቤታችን በስደት ዘመኗ በጣና ቂርቆስ ገዳም የ3 ወር ከ10 ቀን ቆይታዋን አጠናቃ ወደ ገሊላ ናዝሬት ይመለሱ ዘንድ ይመራቸው የነበረው መልዓኩ ገብርኤል ለአረጋዊ ዮሴፍ በህልም ተገልጦ “ህፃኑን እና እናቱን ይዘህ ወደ አገራችሁ ሂዱ” ብሎ ስለነገረው ቅዱስ ዮሴፍም ወደ ህፃኑ በመቅረብ “ፀአና በደመና” (በደመና ጫናት) ባለው ጊዜ የገዳሙና የሃይቁ ስም ጣና ተባለ ተብሎ ይተረካል፡፡
የኮሌራ በሽታ መንስኤውና መከላከያው
ኮሌራ ‹‹ቪብሪዮ ኮሌራ›› በሚባል መርዛማ ባክቴሪያ የሚመጣ የአንጀት ኢንፌክሽን ሲሆን አጣዳፊ ተቅማጥ የሚያስከትል በሽታ ነው። እንደ የአለም ጤና ድርጅት መረጃ በአለም ዙሪያ ከ1 ነጥብ 3 እስከ 4 ሚሊዮን የሚገመቱ ሰዎች በየአመቱ በኮሌራ እንደሚያዙና ከእነዚህም መካከል ከ21ሺ እስከ 143ሺ የሚደርሱ ሰዎች ደግሞ በዚህ በሽታ ለሞት ይዳረጋሉ፡፡
