ኃላፊው ይህንን ያሉት በገቢ አሰባሰብ አፈጻጸም እና ተግዳሮቶች ዙሪያ ከሰሜን ወሎ ዞን፣ ከወልድያ ከተማና ከአካባቢው ወረዳዎች የገቢ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው።
በመድረኩ ላይ ዶክተር መንገሻ እንደገለጹት፤ የክልሉ የገቢ አሰባሰብ ሁኔታ በቀጥታ በልማት ፕሮጀክቶችና በሰራተኞች ጥቅማጥቅም ላይ ተጽዕኖ አለው። በመሆኑም መንግስት የጣለውን ግብ ለማሳካትና የክልሉን የገቢ አፈጻጸም ከፍ ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትጋት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከአፈጻጸም አኳያ የወልድያ ከተማ አስተዳደር እያሳየ ያለው ውጤት የሚበረታታ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፤ በአንጻሩ የሰሜን ወሎ ዞንና የአንዳንድ ወረዳዎች አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆኑን ጠቁመው ክፍተቶቹ ሊታረሙ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው፤ የክልሉን የገቢ እቅድ ለማሳካት በሙሉ አቅማቸው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።
በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ፤ የገቢ አሰባሰቡን ለማሻሻል የተነሱ ጠቃሚ ሃሳቦች በሂደት ተግባራዊ እንደሚደረጉና ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽ ለመስጠት ጥረት እንደሚደረግ ተመላክቷል።
በዚህ የምክክር መድረክ ላይ የወልድያ ከተማ አስተዳደር፣ የክፍለ ከተሞች፣ የጉባላፍቶ ወረዳ እና የሰሜን ወሎ ዞን የገቢ ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
ወልድያ ኮሙኒኬሽን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Ticktock: https://www.tiktok.com/@amharacommunication…


