ርዕይ
ተልዕኮ
ተልዕኮ
በኅብረተሰቡ መካከል ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ በመሠረታዊ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ዙሪያ የመላውን ህዝብ ግንዛቤ በማዳበር ሁለንተናዊ ዕድገታቸንን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር ለርዕያችን ስኬታማነት የተቀናጀ ርብርብ ማድረግ፡፡
እሴቶች
የአማራ ክልል የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ በሚተገበርበት ሂደት ሁሉ የሚከተሉትን እሴቶች ይኖሩታል፡፡
የተመረጡ እሴቶችን (ሙያዊ ብቃት፣ አገሌጋይነት፣ ባህሌን መጠበቅ፣ ሕግን ማክበር፣ ሕዜባዊ ወገንተኝነት፣ አርበኝነት፣ ሀብትን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም፣ ሇሌዕሇ ሏሳብ ተገዢነት፣ ግብ ተኮር፣ ብዜሏነትን መቀበሌ፣ ምርምርና ፇጠራ፣ ቅንጅታዊ አሠራር አና ግሌፅነትና ተጠያቂነት) ሁለም አካሌ ይዝ እንዱተገብራቸው ማድረግ፣
- እውነተኛነት፤
በዚህ ስትራቴጅ ውስጥ ተካተው የሚተገበሩ ሥራዎች ሁሉ እውነት ላይ ብቻ የቆሙ እንዲሆኑ ይደረጋል፣
- ቀዳሚነት፤
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን የሥራ ባህሪ የመረጃ የበላይነትንና መቅደምን የሚጠይቅ በመሆን ቀዳሚነት እንደ ቁልፍ እሴት ይወሰዳል፡፡
- ቅንጅታዊ አሰራር፤
በእቅዱ ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድርሻ ያላቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ እና ተናበው የሚሰሩበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
- አንድነት፤
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራው የአማራ ክልል ህዝብ እና አገራዊ አንድነትን የሚያጠናክርና ነጣይ አካሄዶችን አምርሮ የሚታገል ሆኖ ይሠራል፡፡
- ምርምርና ፈጠራ፤
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ ከዘወትራዊና ተለምዷዊ አካሄድ የወጣና ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ ስልቶችን እና ቻናሎችን ከክልሉ ታላሚ ተደራሾች ባህሪ አኳያ ተንተኖ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
- ብዝሃነትን ማክበር፣
የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ስራዎች የባህል፣ የቋንቋ፣ የማንነት፣ የእምነት፤ የአመለካከት እና የመሳሰሉ ብዝኃነትን የሚያከብር፣ የሚያስተናግድና የሚያካትት ይሆናል፡፡
የአሠራር መርሆዎች፣
- አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ውጤታማ እናደርጋለን፣
- የዜጐች አመኔታና እርካታ የውጤታችን መለኪያ ይሆናል፤
- ከተቋሙ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በጋራ እንሠራለን፣
- የሥራ ተነሳሽነትን መልካም ሥነ-ምግባርንና አርአያነትን በማሳደግ የቡድን አሠራርን እናጠናክራለን፣
- ለምርምርና ጥናት ትኩረት በመስጠት የአፈፃፀም ውጤታማነታችንን እናሣድጋለን፣
- የተሟላ፣ ፈጣንና እኩል አገልግሎት የሚሠጥ፣አደረጃጀት በመገንባት የመረጃ ተጠቃሚነት አመኔታን እናሳድጋለን፣
የባለብዙ ዘርፍ ተግባራትን በበጀት በመደገፍ ዘላቂና ቀጣይነት ያለው ተግባር እንፈጽማለን፡፡
የቢሮው ስልጣንና ተግባር
በክላልች ሕጎች አስቀድሞ የተደነገገው ወይም ወደፊት የሚደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ
የክልሉ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዲዮች ቢሮ የሚከተለት ዝርዝር ሥሌጣን እና ተግባራት
ይኖሩታሌ፡
1/ ፖሉሲዎችን፣ ስትራቴጅዎችን እና ሕጎችን ያመነጫል፣ አፈፃፀሙ ከክልሉ የሌማት
አቅጣጫዎች ጋር የተጣጣመ ዝርዝር መርሃ ግብር ያዘጋጃል፣ ሲፀድቅም ተግባራዊ
ያደርጋል፤
2/ የክልሉ መንግሥት ዋና ቃል አቀባይ በመሆን ይሰራል፣ መንግሥታዊ መልዕክቶችን
ያሰራጫል፣ በክልላዊ ጉዲዮች ላይ የክልሉን መንግሥት ውሳኔዎች እና አቋሞች
ለሕዝብ ይፋ ያደርጋል፤
3/ በክልሉለ መንግሥት አቋሞች እና አሠራሮች ላይ የሚሰነዘሩ ትችቶች እና የሚሰጡ
አስተያየቶችን በንቃት ይከታተላል፣ የሕዝብ አስተያየቶችን በማሰባሰብ እና
በመተንተን ውጤቱን ጉዲዩ ለሚመለከታቸው የክልሉ መንግሥት አካላት
ያሰራጫሉ፤
4/ የክልሉን ሕዝብ እና መንግሥት ጥቅም በማስጠበቅ የሀገር ውስጥ እና የውጭ
መገናኛ ብዘሃን የዕለት ተዕለት የሚዲያ ዲሰሳ ያደርጋል፣ ይተነትናል፣ ጉዲዩ
ለሚመለከታቸው የክልሉ መንግሥት አካላት ያሳውቃል፤
5/ በክሌለ መንግሥት ፖሉሲዎች እና ስትራቴጅዎች ዘሪያ ተገቢውን ግንዚቤ በማስያዝ
እና ግሌፅነትን በማስፈን ሕዝባዊ የውይይት እና የምክክር መድረኮችን ያዘጋጃል፣
ያስተባብራል፤
6/ በክልሉ መንግሥት ስም የመረጃ መረብ ሥራዎችን ያከናውናል፣ የድረ ገጽ
ልውውጦችን ያካሂዲል፤
7/ የክልሉን ሕዝብ እና መንግሥት ሁነቶች አስመልክቶ በክልሉ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ
በውጭ ሀገር ጋዛጠኞች በየወቅቱ መግለጫዎችን ይሰጣል፤
8/ የክልሉን ሕዝብ እና መንግሥት መልካም ገፅታ ለመገንባት የሚያስችል ተከታታይ
ሥራዎችን ይሰራል፣ መረጃዎችን ይሰጣል፣ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎች
በወቅቱ እንዲታረሙ ያደርጋል፤
9/ ከሚመለከተው አካላት ጋር በመሆን ከክልሉ ህዜብ ባህል፣ እሴት እና ታሪክ ውጭ
በሆነ አግባብ በክልሉ ህዝብ ላይ የሚነሱ የሀሰት ትርክቶች እንዲታረሙ ተገቢ
የሆኑ ሥራዎችን ይሠራል፣ ሀሰተኛ ትርክቶችን ይከላከላሌ፣ ብሔራዊ ገዥ ትርክት
እንዱሰርፅ በማድረግ በትኩረት ይሰራል፤
10/ በመንግሥት እና በሕዝብ መካከል የሚደረጉ የተግባቦት ግንኙነትን ያስተዲድራል፤
በመንግሥት ባለሥልጣናት እና በህብረተሰቡ መካከል ውይይቶች እንዲካሄዱ
መድረኮችን ያመቻቻል፤
11/ የመንግሥት ተግባራትን እና የሌማት ዕቅድችን ለሕዝብ በትክክል በማስገንዘብ
ከሚያያዎች ጋር ግንኙነቶችን ይፈጥራል፣ ጋዛጣዊ መግለጫዎችን ያዘጋጃል፣
የተቋማት የሚዲያ ጥያቄዎች ወቅታዊ እና ተገቢ ምላሽ ይሰጣል፤
12/ በድንገተኛ ሁኔታዎች ወይም በቀውሶች ጊዜ የሰላም ጋዜጠኝነትን የሚያጎላ
የግንኙነት ስሌቶችን ያዘጋጃል፣ ለሕዝቡ ትክክለኛውን መረጃ ያሳውቃል፣ የተሳሳቱ
መረጃዎች ሲያጋጥሙ በማረም በንቃት ይሠራል፤
13/ የመንግሥትን የሌማት ውጥኖች እና ተነሳሽነቶች የሚያንፀባርቁ እና ሕዝባዊ
ተሳትፎን የሚያበረታቱ መጣጥፍችን፣ ቪዲዮዎችን፣ ብሮሸሮችን እና የማህበራዊ
ሚዲያ ዘመቻዎችን ጨምሮ አሳታፊ ይዘቶችን ያዘጋጃል፣ ለህብረተሰቡ ተደራሽ
እንዱሆኑ ያደርጋሌ፤
14/ ሁለም የተግባቦት ጥረቶች ከመንግሥት አጠቃላይ ተልዕኮ እና ከማህበረሰቡ
እሴቶች ጋር ተጣጥመው እንዲፈፀሙ ያደርጋል፤
15/ የተለያዩ የመንግሥት አካላት በውጤታማ የተግባቦት ስሌቶች እና የሚዲያ
መስተጋብር ላይ የአቅም ግንባታ ሥልጠና ይሰጣል፣ መልዕክቶችን በግልፅ እና
በውጤታማነት እንዲተላለፉ እገዛ ያደርጋል፤
16/ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የኮሚዩኒኬሽን እና የመረጃ ስርጭትን
በተመለከተ አንዴ ወጥ አሠራር እንዲኖር በማድረግ ሥርዓት ይዘረጋል፣
አፈፃፀሙንም ይከታተላሉ፤
17/ በመንግሥት ሴክተሮች ውስጥ የሚከናወኑ የተግባቦት ሥራዎችን ያቀናጃሉ፣
ይከታተላሉ፣ የሚቀርቡ ሪፖርቶችን ይገመግማል፣ ድጋፍ እና ክትትል ያደርጋል፤
18/ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና ሚዲያ የሥራ መነሻ
የሚሆን አጀንዳ ይቀርፃል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፤
19/ ከሚመለከተው የፋደራል መንግስት አካል ጋር በመተባበር ሥርጭታቸው በክልሉ
ውስጥ ሆነ እና ለንግድ ዓላማ የሚውለ የህትመት ሚዲያ እና ማስታወቂያ ሥራ
በሚሰማሩ አካላት ፈቃድ ይሰጣል፣ በሕጉ መሠረት መስራታቸውንም ይከታተላል፣
ይቆጣጠራል፤
20/ በክልሉ ውስጥ የሚታተሙ የውጭ ወይም የአደባባይ ማስታወቂያዎችን
አስመልክቶ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ስታንዲርድ ያወጣል፣ ሥራ
ላይ ያውላል፣ ይከታተላልሌ፣ ይቆጣጠራል፤
21/ በክልሉ ርዕሰ መስተዲድር በሚሰጠው ውክልና መሠረት የክልሉን መንግስት
ተቋማት የሕዝብ ግኑኝነት ኃላፊዎች ሹመት ይሰጣል፣ የስራ አፈፃፀማቸውን
ይከታተላል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከኃላፊነት ያነሳል፤
22/ በክልሉ ውስጥ የውጭ ወይም የአደባባይ ማስታወቂያ የሚለጥፍ አካሊት ፈቃድ
ያላቸው መሆናቸውን ያረጋግጣል፣ ይቆጠራል፤
23/ ከሚመለከተው ጋር በመሆን የውጭ ወይም የአደባባይ ማስታወቂያዎች
የህብረተሰቡን ባህል፣ እሴቶች እንዱሁም የተግባቦት መርሆዎች የጠበቁ መሆናቸውን
ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ እርምጃ ይወስዲል፣ ያስወስዲል፡፡
