የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበርን የምዝገባ እና የቦታ ዝግጅት ስራዎችን ገመገመ፤
ክቡር ከንቲባ አቶ ጎሹ እንዳላማው ከከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ጋር የመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበርን የምዝገባ እና የቦታ ዝግጅት ስራዎችን ገምግመዋል።
በመኖሪያ ቤት ህብረት ስራ ማህበር ለመደራጀት 22 በሽህ 847 ዜጎችን መመዝገብ የተቻለ ሲሆን የምዝገባ ሂደቱም እጅግ ዘመናዊ በሆነ ሲስተም የተከናወነ፣ በጥብቅ ዲስፕሊን የተመራ፣ ከደላላ በፀዳ መንገድ የተከናወነ ተግባር ነው በአጠቃላይ በጥሩ የስራ ዲስፕሊን ሁኔታ የተመራ እና ተሞክሮ በሚሆን መንገድ የተተገበረ የምዝገባ ስራ መከናወኑ በግምገማው ተረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ቤት ፍላጊዎች ትዳር እያላቸዉ ያላገባ መረጃ በማፃፍ፣ በሀሰት ጋብቻና ፍች ማስረጃዎች፣ በፎርጅድ ማስረጃ፣ ሁለት አመት ሳይሞላቸዉ በተሳሳተ የነዋሪነት ማስረጃ፣ ቦታ እያላቸዉ ተጨማሪ ቦታ ለመዉስድ የተመዘገቡ በመሆኑ እጅግ አደገኛ ዝንባሌ መኖሩን በዝርዝር ተገምግሟል፡፡
እነዚህን ጥሩ ያልሆነ ዝንባሌ ወደ ማጣራት ከመገባቱ በፊት በዚህ የምዝገባ ሂደት የታዩ ጥንካሬዎችና ክፍተቶችን ጨምሮ የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ሀላፊዎች እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በዝርዝር እንዲገመገም ወስኗል፡፡
በዚህ የግምገማ ሂደት ተቋማት የሰጡትን ማስረጃ አንድ እድል ብቻ ተሰጧቸዉ እንደገና በዝርዝር ገምግመዉ የሚያስተካክሉበት እና ትክክለኛና የሚገባቸዉ ዜጎች ብቻ ተደራጅተዉ ተጠቃሚ የሚሆኑበት እድል እንዲፈጠር ይደረጋል፡፡
ይህ ግምገማ ከተከናወነ በኋላ ዝርዝር የማጣራት እቅድ ተዘጋጅቶ በፍጥነትና በጥራት የማጣራትና የማደራጀት እንዲሁም እውቅና የመስጠት ስራ እንዲከናወን አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የቦታ ዝግጅቱም በተቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት በአራቱም አቅጣጫ ቦታ የማዘጋጀት፣ ተነሽዎችን የመለየት፣ የሳይት ዝግጅት ወዘተ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጥሩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ኮሚቴዉ ገምግሟል፡፡
በዚህ ሂደት የነበሩ መዘገየቶች በፍጥነት ታርመዉ በአራቱም አቅጣጫ የሚደረገዉ የቦታ ዝግጅት ከማደራጀት ስራዉ እኩል እንዲጠናቀቅና ዜጎችን በአጭር ጊዜ ቦታ የማስረከብ ስራ እንዲሰራ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡
የመጀመሪያዉን ምዕራፍ በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ የባህርዳር ከተማ የዲጅታል መታወቂያ ዝግጅት የተጠናቀቀ በመሆኑ በቅርብ የህብረተሰቡን እና የግል ድርጅት ሠራተኞችን የመመዝገብና የማደራጀት ስራ የሚጀመር ይሆናል፡፡
መረጃው ባሕርዳር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።
ተጨማሪተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Ticktock: https://www.tiktok.com/@amharacommunication…
Website: https://www.amharacomm.gov.e
