የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የአስፈፃሚ አካላትን እንደገና ማቋቋሚያ እና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ አፀደቀ።
ሶስተኛ ቀነኑ የያዘው የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሻሻለው የአስፈፃሚ አካላትን እንደገና ማቋቋሚያ እና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ አጽድቋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔ የፀደቀው የአስፈፃሚ አካላትን እንደገና ማቋቋሚያ እና ሥልጣንና ተግባራት መወሰኛ አዋጁ :-
የሕግ የበላይነት በማረጋገጥ በክልሉ ያሉትን የመልማት ፀጋዎች አውጥቶ ለመጠቀምና ለዘመናት ስር ሰደው የቆዩትን የድህነትና የግጭት አዙሪቶች በማስቀረት የትውልዶች ጥያቄ የነበረውን ብልፅግናን እውን ለማድረግ መንግሥታዊ ተቋማትን ፈትሾ እንደገና ማደራጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤
ላለፉት በርካታ ዓመታት የተሸረሸሩ ጠቃሚ ክልላዊ ወጎችን፣ እሴቶችንና ባህሎችን መልሶ በመገንባትና ስብራቶችን በመ በመጠገን በስነምግባር የታነፀና አገር ወዳድ ትውልድ የማፍራት ወሳኝ ተልዕኮ የሚሸከም ውጤታማ ተቋማት ለመፍጠር የተቋማትን አደረጃጀት እንደገና ማሻሻል የሚገባ መሆኑ ስለታመነበት ፤
ምርታማነትንና ቅልጥፍናን በማሳደግ ጥራት ያለው ኢኮኖሚ ለመገንባትና በክልሉ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ የሚካሄዱ ፈርጀ ብዙ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች በመላ የክልሉ ሕዝብ ዘንድ ዘላቂ ቅቡልነት ኖሯቸው እንዲከናወኑ ለማድረግ በሚችሉ ተቋማዊ የማሻሻያ እርምጃዎች ማጀብ እና መደገፍ ተገቢ በመሆኑ፤
የተሻሻለው የአስፈፃሚ አካላት እንደገና ማቋቋሚያ፣ ሥልጣን እና ተግባራት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር 280/2014 ላይ ተፈጥረው የነበሩትን ክፍተቶች ቀርፎ ተቋማት ሲደራጁ ከሌሎች ተቋማት ሥልጣንና ተግባር ጋር የማይጋጭ ግልፅ ዓላማ ይዘው እንዲደራጁ ለማድረግ ተግባርና ኃላፊነታቸውን ለመወጣት በቅንጅት መሥራትና ውጤታማነትን ማሳደግ እንዲችሉ፣ ኃላፊነታቸውን ሲያጓድሉ ደግሞ ተጠያቂነትን ለማስፈን እንዲቻል የአስፈፃሚ አካላትን አደረጃጀት እንደገና ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤
ከዚህ በፊት የነበሩት የአስፈፃሚ አካላት አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር መወሰኛ አዋጆች በፍጥነት በመለዋወጣቸው ምክንያት ተፈጥረው የነበሩትን የተቋማት አደረጃጀቶች እና የስያሜ ወጥነት ችግሮች በመቅረፍ ወጪ ቆጣቢ እና የመፈፀም አቅማቸው ያደገ፣ የተረጋጋ እና ተቋማዊ ትውስታ ያለው ተቋም ለመፍጠር፣ ከማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጦች ጋር አብረው እየተለወጡና ራሳቸውን እያሻሻሉ የሚሄዱ ዘመኑን የዋጁ ተቋማትን ማደራጀት አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ፤
አስፈፃሚ አካላት ተገልጋዩን ኅብረተሰብ የሚያረካ የተቀላጠፈ ውሳኔ ለመስጠት እንዲችሉ የሥራ ቀረቤታ፣ የተልዕኮ ትስስር እና እርስ በእርስ ተመጋጋቢና ተያያዥ ባህሪይ ያላቸውን የተበታተኑ የሥራ ዘርፎች አሰባስቦ በአንድ አስፈፃሚ አካል ስር ማጠቃለል እንዲሁም ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግሥት አቻዎቻቸው ጋር ተናባቢ እንዲሆኑ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ፤
የተጀመረውን መሠረታዊ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ አፋጥኖ በክልሉ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማትን ለማስፋፋትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ክልሉ ያሉትን እምቅ ሰብዓዊና ቁሳዊ አቅሞች ተጠቅሞ ያሉበትን መሠረታዊ ተግዳሮቶች እንዲሻገርና ዘላቂ ልማት እንዲረጋገጥ ለማድረግ ለዚህ ወሳኝ አጀንዳ የሚመጥኑ የተቋማት አደረጃጀቶችን መፍጠር በማስፈለጉ፤
ለፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገት መሠረት መሆን የሚችል አምራች ሰብዓዊ ሀብት ለማልማት እንዲሁም ሕዝብን ለማገልገልና ክልሉን ለማበልፀግ ሙያዊ ኃላፊነታቸውን በብቃት የሚወጡ በዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ የተቃኙ አገልጋይና ሥልጡን ሲቪል ስርቫንቶችን ለማፍራት የተቋማትን አደረጃጀቶች እንደገና ማሻሻል አንገብጋቢ አጀንዳ ሆኖ በመገኘቱ የአማራ ክልል ምክር ቤት በተሻሻለው የብሔራዊ ክልሉ ሕገ-መንግሥት አንቀፅ 49 ንዑስ አንቀጽ 3 (1) ድንጋጌ ስር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህንን አዋጅ ማውጣቱ በጉባኤው ተገልጿል።
የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር፣ 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔው የሦስተኛ ቀን የጉባዔ ውሎ እያካሄደ ይገኛል።
