የአማራ መንገድ ቢሮ የህዝብ ግንኘነት ኃላፊ
“በፍኖተሰላም ከተማ የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች አበረታች ናቸው”
የአማራ መንገድ ቢሮ የህዝብ ግንኘነት ኃላፊ
በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተሰላም ከተማ አስተዳደር የተጀመሩ የመሠረተ ልማት ስራዎች አበረታች መሆናቸውን የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በትግሉ ተስፋሁን ዛሬ በፍኖተሰላም ከተማ ባደረጉት የመስክ ጉብኝት ተናገሩ።
በፍኖተሰላም ከተማ አስተዳደር ከተቋማት ግቢ ማስዋብ እስከ አደባባይ እድሳትና ጥገና የተጀመረው መነሳሳትና በከተማው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ላይ በማህበረሰብ ዘንድ የአስተሳሰብ ለውጥና መነሳሳት የፈጠረ መሆኑን በዞን ደረጃ በፈጠርናቸው መድረኮች ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ የአማራ ክልል መንገድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ገልጸዋል።
አቶ በትግሉ ፍኖተሰላም ከተማ በዕድሜ ደረጃ ረጅም ዕድሜ ካላቸው ከተሞች ተርታ የምትመደብ ከተማ ሆና እያለ ግን እንዳትንቀሳሽ ተብላ የተነገራት ይመስል በልማት ተጠቃሚነቷ ወደ ኋላ ብላ የቆየች ከተማ ቢሆንም ከቅርብ አመታት ወዲህ የልማት እንቅስቃሴዋ እየጎመራና እየተሻሻለ የመጣ ነው።
በቀጣይም የኮሪደር ልማት መነሻ የሚሆኑ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ዛሬ በከተማ አስተዳደሩ ተቋማትና በታሪካዊው የፍኖተ ሰላም ከተማ አደባባይ የተጀመሩ ስራዎች ፣ የፍኖተ ሰላም አዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ እና የሪፈራል ሆስፒታሉ ግንባታ ስራ እንደገና የመጀመር ስራ የተሄደበት ርቀት አበረታች ስለሆነ ተጠናክረው ይቀጥሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አቶ በትግሉ ተስፋሁን አስተላልፈዋል።
