



ለ34ኛ ዙር ተመራቂ የአድማ መከላከል ፓሊስ አባላት አቀባበል ተደረገላቸው፤
በሰሜን ጎንደር ዞን ስተዳደር በደባርቅ ከተማ ለ34ኛ ዙር ተመራቂ የአድማ መከላከል ፓሊስ አባላት በ11ኛ እና በ13ኛ ሻለቃ አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ተደርጎላቸዋል።
በአማራ ፖሊስ የሰሜን ጎንደር ዞን አድማ መከላከል የ11ኛ ሻለቃ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ነጋሽ አየነው እና የ13ኛ ሻለቃ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ቢራራ አዳነ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የ34ኛ ዙር ተመራቂ አባላት ከነባሩ የ11ኛ እና የ13ኛ ሻለቃ የአድማ መከላከል አባላት ጋር መቀላቀላቸው የአካባቢውን ሠላም የበለጠ ለማረጋጋት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
አዲስ ተመራቂ የአድማ መከላከል ፖሊስ አባላትም ከነባሮቹ አባላት ጋር መቀላቀላቸው እንዳስደሰታቸው ገልፀው ከበፊቱ በተሻለ መንገድ ግዳጃቸውን ለመፈፀም እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል።
መረጃው የሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Ticktock: https://www.tiktok.com/@amharacommunication…
Website: https://www.amharacomm.gov.et
