

” የባሕልና የኪነጥበብ ፌስትቫሉ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የሚጠናከርበት መድረክ ነው ” መልካሙ ጸጋዬ
16ኛው የአማራ ክልል የባሕል እና የኪነ ጥበብ ፌስቲቫል ”ድንቅ ምድር ድንቅ ባሕል” በሚል መሪ መልዕክት በጎንደር ከተማ እየተከበረ ሰንብቷል። ዛሬ ደግሞ የማጠቃለያ ዝግጅቱ እየተካሄ ነው።
በማጠቃለያ መርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተለላፉት የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ጸጋዬ ፌስቲቫሉ ከተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የመጡ የባሕል ቡድኖች ልምድ የሚለዋወጡበት፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የሚጠናከርበት መድረክ መኾኑን ገልጸዋል።
የሙዚቃ እና ቲያትር፣ የስዕል እና ቅርጻ ቅርጽ አውደ ርዕይ፣ የጥበብ አውደ ርዕይ እና ሌሎችም ዝግጅቶች ሲቀርቡ መሰንበታቸውን ጠቅሰዋል።
የባሕል እና የኪነ ጥበብ ዘርፉን ከፍ በማድረግ የሕዝባችን ልዕልና ከፍ ለማድረግ እና ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ያለመታከት እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።
ባሕሉ የጋራ ሀብታችን መኾኑን በመገንዘብ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ሊጠብቀው፣ ሊያለማው እና ለመጪው ትውልድ ሊያስተላልፈው ይገባል ነው ያሉት።
በፌስቲቫሉ የአጎራባች ክልሎች የባሕል ቡድኖች ተሳትፈውበታል።
አሚኮ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Website: https://www.amharacomm.gov.et