የከተራና የጥምቀት በዓል በአማራ ክልል በሁሉም አካባቢዎች በሰላም መከበሩን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የከተራና የጥምቀት በዓል በአማራ ክልል ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን በጠበቀ መልኩ፣ በድምቀት እና በሰላም መከበሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ዋና ኀላፊ ምክትል ኮማንደር መሳፍንት እሸቴ የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች በድምቀት እና በሰላም መከበራቸውን ገልጸዋል።
በዓላት ያለአንዳች የጸጥታ ችግር ተከብረው እንዲውሉ ለማስቻል ዝግጅት ተደርጎ ነበርም ብለዋል። ከሃይማኖት አባቶች፣ ከወጣቶች እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደርጎ ነበር፤ ይህም ሁሉም የሰላሙ ባለቤት ኾኖ በሰላም ለማሳለፍ አስችሏል ነው ያሉት።
በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከጸጥታ አካላት ጋር በመኾን የአካባቢያቸውን ሰላም ሲያስጠብቁ የነበሩ ወጣቶችንም አመስግነዋል።
