
የከተራ እና የጥምቀት በዓል በመላው የአማራ ክልል አካባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል።
***********
የዘንድሮው የከተራና የጥምቀት በዓል በመላው የአማራ ክልል አካባቢዎች ደማቅ ሁኔታ ሲከበር ውሏል። የከተራ በዓል ከትናንት ጀምሮ ታቦታት ከየአብያተ ክርስትያናቱ ተነስተው ወደ ባህረ ጥምቀቱ በመሄድ አድረዋል።
በዛሬው ዕለት ደግሞ በየባህረ-ጥምቀቱ ልዩ ልዩ መልዕክቶች ተላልፈውና ስርዓተ-ጥምቀቱ ተከናውኖ በዓሉ በድምቀት ተከብሯል።
በዓሉ በሁሉም አካባቢዎች ባህላዊና ሀይማኖታዊ ይዘቱን ጠብቆ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከብሮ ውሏል። በነገው ዕለትም የቃና ዘገሊላ በዓል ይከበራል።
ስለሆነም ይህ ታላቅ የአደባባይ በዓል በሰላማዊ መንገድ በድምቀት እንዲከበር አስተዋፅኦ ላበረከታችሁ ለመላው የፀጥታ አካላት፣ በየደረጃው ላስተባበራችሁ የባህልና ቱሪዝም መዋቅሮቻችን፣ ለመላው የህብረተሰብ ክፍል ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።