

የጥምቀት በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጂት ተደርጓል።
መጪውን የጥምቀት በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር የከተማው ፖሊስ የዝግጅት ስራውን በማጠናቀቅ ወደ ስራ መገባቱን የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አበባው አሻግሬ ተናገሩ።
በወርሃ ጥር የሚከበሩ የአደባባይ በዓላትን የተመለከተ የምክክርና የኦሬንቴሽን መድረክ በደሴ ከተማ ተካሂዷል።
በመድረኩ በዓላቱን ሃይማኖታዊ ይዘታቸውን ጠብቀው በሰላም እንዲከበሩ የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ደህንነት መምሪያ ምክትል ሀላፊ ኢ/ር አዳነ የእቅድ ኦሬንቴሽኑን ያቀረቡ ሲሆን በገለፃቸውም የፀጥታ መዋቅሩ በቅንጅት በመስራት የከተማዋን ሰላም ማስጠበቅ መሆኑን በመረዳት በዓላላቱን ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ሰኢድ አሊ ከህብረተሰቡ ከንግድ መምሪያ ከመብራት ሃይል ከውሃ ልማት ጤና መምሪያ እንዲሁም የፀጥታ መዋቅሩ በጋራ ለበአሉ በሰላም መጠናቀቅ የቅድመ ቅንጅት ስራ መሰራቱን ገልፀዋል ።
የከተማው ፖሊስ መምሪያ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀትት በትብብር በመስራት በዓሉ በሰላም እንዲከበር የቅድም ዝግጅት ተግባራትን በማጠናቀቅ ወደ ስራ መገባቱን የደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር አበባው አሻግሬ ገልፀዋል።
እንደ ኮማንደር አበባው ገለፃ በዓላቱ የአደባባይ በዓላት እንደመሆናቸው የፀጥታ አካላት በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች ስምሪት በመስጠት ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር ዝግጅት ተደርጓል።