
የፋሲል አብያተ መንግስታት ጥገና እና እድሳት የቅርሱን ይዘት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡
የፋሲል አብያተ መንግስታት ጥገናና እድሳት የቅርሱን ይዘት ጠብቆ እየተከናወነ ነው” ሰላማዊት ካሳ
የፋሲል አብያተ መንግስታት ጥገና እና እድሳት የቅርሱን ይዘት በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑን የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ገለጹ፡፡
ሚኒስትሯ በጎንደር ቆይታቸው ጥምቀትን ለማክበር ከተገኙት የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተወካይ ጋር በፋሲል አብያተ መንግስት የተደረገውን የቅርስ ጥበቃና የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ሥራ መጎብኘታቸውን ተናግረዋል፡፡
እድሳቱ ከ80 ያላነሱ የቅርስ ጥበቃ ባለሞያዎች ዝርዝር ጥናት ላይ ተመስርቶና ለዓመታት ከተደረገ ዝግጅት በኋላ የተከናወነ መሆኑ ለቅርሱ የተሰጠውን ትኩረት እንደሚያመላክት ገልጸዋል፡፡
አንድ ቅርስ በዩኔስኮ መመዝገቡ ቅርሱ ያለውን ይዘት ጠብቆ ተገቢ ጥገና እና እድሳት እየተደረገለት ለትውልድ እንዲተላለፍ ማድረግ መሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም የፋሲል አብያተ መንግስታት እድሳት በዚሁ አግባብ የተከናወነ እና ስኬታማ ስራ መሆኑን ነው የተናገሩት፡፡
በሒደቱም ኢትዮጵያ የዩኔስኮ አባል ሀገር እንደመሆኗ ለፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች ተፈጻሚነት በሀገራችን በኩል ለተቋሙ ተወካይ በሆነው የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን በኩል ተሳትፎ ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡


