
የጥምቀት በዓል በሰላም መጠናቀቁን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ገለጸ
ጎንደር ለወራት ቅድመ ዝግጅት ሥታደርግበት የቆየችውን የ2017 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በሰላም ማጠናቀቋን የከተማ አሥተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው ገልጸዋል።
ከቅርብም፣ ከሩቅም፤ ከሀገር ውስጥም ከውጭም ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር በርካታ እንግዶች ወደ ጥንታዊቷ እና ታሪካዊቷ ከተማ ጎንደር መግባታቸውንም አስታውቀዋል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን እና የውጭ ሀገር ዜጎች የተሳተፉበት የጥምቀት በዓል በሰላም መጠናቀቁንም ነው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የገለጹት።
ጥር 12/2017 ዓ.ም የቃና ዘገሊላ በዓል በከተማ አሥተዳደሩ በድምቀት እንደሚከበር ጠቁመው እንግዶች ቢሳተፉ የጎንደርን እሴት እና እንግዳ ተቀባይነት በስፋት ይመለከቱበታል ብለዋል።
የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲጠናቀቅ እገዛ ላደረጉ ወጣቶች እና የጸጥታ አባላት ምሥጋና ማቅረባቸውን ከአስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል።