ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ የተገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ገቡ።
የአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት አመት በመንግስትና በረጅ ድርጅቶች የተገነቡ 176 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ተግባር ገብተዋል።
በ2 ቢሊዮን 888 ሚሊዮን 808 ሺህ ብር የተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶች 22 ሺህ 755 ለሚሆኑ አባወራ እና እማወራዎች ጥቅም ይሰጣሉ ተብሏል።
አቶ ጌትነት አያሌው በቢሮው የመስኖና ድሬኔጅ ግንባታ ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለፋና ሚዲያ ክርፖሬሽን እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በርካቶችን የመስኖ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ማስገባት ተችሏል ብለዋል።
ለዚህ ስኬት ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር እና ባለሙያ ያደረገው ጥረት ከፍተኛ እንደነበር ያነሱት አቶ ጌትነት ተገንብተው የተጠናቀቁ የመስኖ ፕሮጀክቶች አርሶአደሩ ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ በኩል ጉልህ ድርሻ አላቸው።
ደሴ ፋና
