
ለሰላም እየተጉ የሚገኙ ብርቱ ክንዶች በደብረ ኤልያስ ወረዳ ![]()
“በወረዳው አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን እውን ለማድረግ ከመቸውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ነን” የሰላም አስከባሪ አባላት
በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ኤልያስ ወረዳ የሰላም አስከባሪው ሀይል የሚሰጠውን ማንኛውንም የህግ ማስከበር ተልዕኮ በውጤት በመፈፀም አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን እውን ለማድረግ በተሟላ ዝግጁ ላይ መሆኑን የወረዳው ሚሊሻ ጽ/ቤት አስታወቀ።
የወረዳው ሠላም አስከባሪ ኃይል የስነ ልቦና ግንባታ ስልጠና ተሰጥቶ ለቀጣይ ተልዕኮ ዝግጁነቱን የሚያረጋግጥ ወታደራዊ የሰልፍ ትሪኢት በዛሬው እለት ተካሂዷል።
የሰላም አስከባሪ አባላቱ እንደተናገሩት፤ በወረዳው የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም በማፅናት አስተማማኝና ዘላቂ ሰላምን እውን ለማድረግ የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ህግ የማስከበር ተልዕኮ ተቀብለው በቁርጠኝነት እንደሚወጡ ተናግረዋል።
በወረዳው የአካባቢን ሰላም በራስ አቅም ለማረጋገጥ የፀጥታ መዋቅሩን በሰው ሃይልና በትጥቅ የማጠናከር ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ከደብረ ኤልያስ ወረዳ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ኮሙኒኬሽን ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጫኑ።
Facebook: http://facebook.com/AmharaCommunications
Telegram ፡ https://t.me/amharacommunications
Twitter: https://twitter.com/Amhara_GCAO
You Tube: https://www.youtube.com/@amharacommunication
Ticktock: https://www.tiktok.com/@amharacommunication…
Website: https://www.amharacomm.gov.e
Amhara Communications ·Follow
eosSrtndop793t1653u6i9m4f0hc31528gm85520t9ghl90mif1524uhct9u ·
ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ የተገነቡ የመስኖ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ገቡ።
የአማራ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ቢሮ በ2017 በጀት አመት በመንግስትና በረጅ ድርጅቶች የተገነቡ 176 ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ተግባር ገብተዋል።
በ2 ቢሊዮን 888 ሚሊዮን 808 ሺህ ብር የተገነቡት የመስኖ ፕሮጀክቶች 22 ሺህ 755 ለሚሆኑ አባወራ እና እማወራዎች ጥቅም ይሰጣሉ ተብሏል።
አቶ ጌትነት አያሌው በቢሮው የመስኖና ድሬኔጅ ግንባታ ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለፋና ሚዲያ ክርፖሬሽን እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ በርካቶችን የመስኖ ፕሮጀክቶች ወደ ተግባር ማስገባት ተችሏል ብለዋል።
ለዚህ ስኬት ከላይ እስከ ታች ያለው አመራር እና ባለሙያ ያደረገው ጥረት ከፍተኛ እንደነበር ያነሱት አቶ ጌትነት ተገንብተው የተጠናቀቁ የመስኖ ፕሮጀክቶች አርሶአደሩ ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ በኩል ጉልህ ድርሻ አላቸው።
ደሴ ፋና
