በተከታታይ ቀናት መንግስት ያደረገላቸዉን የሰላም ጥሪ ተቀብለዉ ለገቡ 467 በላይ ለሚሆኑ የፅንፈኛ ቡድኑ አባላት ለነበሩ ታጣቂዎች አቀባበል ተደረገላቸዉ።
በሰሜን ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ ወረሞ ዋጂቱ ንዑስ ወረዳ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች በተከታታይ ቀናት የመንግስት የሰላም ጥሪ ለተቀበሉ 467 በላይ ለሚሆኑ የፅንፈኛ ቡድኑ አባላት ሀምሌ 06/2017 ዓ/ም አቀባበል ተደርጓል።
የ101ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማቲዎስ ማደቦ እንደተናገሩት የትም ፣መቸም ቢሆን ሰላም አሸናፊ ነው ለሰላም ቅድሚያ በመሥጠት መንግስት ያቀረበው የሰላም ጥሪ በመቀበል ወደ ቀደመ ሰላማዊ ህይት መመለስ መቻላችሁ ብልህነት ነው ብለዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ብልፅግና ፖርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤሊያስ አበበ እንደተናገሩት ትናንት በጥፋት እና በተሳሳተ መንገድ ላይ የነበሩ ዛሬ ላይ የሰላም ጥሪ የተቀበሉ እና ወደ ቀደመ ሰላማዊ ህይዎታቸው የተመለሱ ወንድሞቻችን የተገኘውን አንፃራዊ ሰላም ለማስቀጠል በየ ደረጃው ከሚገኘው የአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በጥምረት በመሥራት የሰላም ባለቤት መሆን ይገባል ሲሉ ገልፀዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ ካሳለፍናቸው አስከፊ የሰላም እጦት ችግሮች ትምህርት በመውሰድ ለሰላም ቅድሚያ በመሥጠት የአካባቢው ማህበረሰብ ያጠውን ሰላም መልሶ እንዲያገኘ ላስቻለን እና ጫካ የነበሩ ወንድሞቻችንን በፍቅር ለተቀበሉ ጥምር ጦር ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን በተደረገው የሰላም ጥሪ ከ467 በላይ የሚሆኑ የፅንፈኛ ቡድኑ አባላት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው አቀባበል የተደረገላቸው መሆኑን አስረድተዋል። አክለውም በቀጣይ ተከታታይ ቀናቶች አጫጭር የአስተሳስብ እና አቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚሰጡ ገልፀዋል።
በመርሀግብሩ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሻ አለማየሁ፣ የብልፅግና ፖርቲ ቅ/ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ኤሊያስ አበበ፣ የ101ኛ አየር ወለድ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል ማቲዎስ ማደቦ ፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ ኢብራሂም ጨምሮ ሌሎች የዞን፣ የወረዳ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት አመራሮች ተገኝተዋል።
