ባህላዊ የእርቅ ስርዓት ዘላቂ ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለጸ፤
ሰሜን ወሎ ዞን በደሴ ዙሪያ ወረዳ ባህላዊ እርቅ ስርዓት በማህበረሰቡ ዘንድ ዘላቂ ሰላምን፣ መልካም አስተዳደርን እና ልማትን ለማረጋገጥ ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን የወረዳው ባህል ቱሪዝም ጽ/አቤት ገለጸ።
የወረዳው የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዱሰላም ሰይድ እንዳሉት፦ በወረዳው 09 ንባር አገር ቀበሌ የጢሮ ረከቦት ባህላዊ የእርቅ ቦታ በወረዳው ካሉ የእርቅ ስርዓት ከሚካሄድባቸው ቦታዎች አንዱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ባህላዊ የእርቅ ስርዓቱ በደም የሚፈላለጉ ሰዎችን ሳይቀር በእርቅ በመጨረስ እንዲሁም በስርቆት፣ በዘረፋ፣ በድብደባና በሌሎችም ማህበራዊ ችግሮች የሚከሰቱ ግጭቶችን በማስቀረት ማህበረሰቡ በሰላም እና በመተባበር የሚኖርበትን መንገድ የሚፈጥር መሆኑን ኃላፊው አስግንዝበዋል፡፡
የባህል እሴት እና ኢንዱስትሪ ልማት ቡድን መሪ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉ ዳምጣው በበኩላቸው፦ በወረዳው ያሉ ባህላዊ የእርቅ ስርዓትን መረጃ የማሰባሰብ እና ፋይዳቸውንም በዝርዝር የማጥናት ስራ እየተሰራ ሲሆን ከዘመናዊው የፍትህ ስርዓት ጋር እንዳይጣራሱ ከሚመለከታቸው የፍትህ ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል::
በደሴ ዙሪያ ወረዳ 09 ንባር አገር ቀበሌ የጢሮ ረከቦት የባህላዊ እርቅ ማከናወኛ ቦታ ላይ እርቅ ለመፈጠም የተገኙት አርሶ አደር አሊ ኢብራሂም እና መሐመድ ሰይድ በሰጡት አስተያየት፦ ባህላዊ የእርቅ ስርዓቱ በማህበረሰቡ በፍርድ ቤቶች ውስጥ ያለውን የሥራ ጫና ከመቀነሱም ባሻገር በሀሰት ምስክር ምክንያት የሚከሰተውን የፍትህ መጓደል የሚያስቀር መሆኑን አብራረተዋል፡፡
አርሶ አደሩ ፍትህን ለማግኙት የሚያባክነውን ጉልበት፣ ጊዜና ወጭ ከማስቀረቱም በሻገር በድብቅና በፊት ለፊት የሚፈፀመው ወንጀሎችን ቀድሞ ለመከላከል እንደሚያግዝም አስረድተዋል፡፡
አባጋር ፋጡማ ይማም በጢሮ ረከቦት አባጋር ሲሆኑ የእርቅ ቦታው ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየ መሆኑን ገልጸው ግጭት ውስጥ የገቡ እና የተጋደሉ ሰዎች እርቅ በመፈፀም ወደ ቀድሞው ማህራዊ ኑሯቸው ሚቀጥሉበትና በታረቁበት ጉዳይ ላይ ተመልሰው ወደ ግጭት የማይመለሱበት የእርቅ ስርዓት መሆኑን አስገንዝበዋል።
መረጃው የደሴ ዙሪያ መንግስት ኮሙኒኬሽን ነው።


