
ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ጎንደር ከተማ ገቡ።
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በጥምቀት በዓል ላይ ለመታደም ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱና አፈጉባኤው ጎንደር አጼ ቴዎድሮስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደን ጨምሮ የክልሉ እና የከተማ አሥተዳደሩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና የማኅበረሰብ ተወካዮች አቀባበል አድርገውላቸዋል